1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን 7 ጉባኤ በጃፓን

ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2008

የ7ቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገራት « G7» ጉባኤ ጃፓን ዉስጥ ቅዱስ ቦታ ተብሎ በሚታወቀዉ «ኤሴ ሺማ » ደሴት ላይ ለሁለት ቀናት በመካሄድ ላይ ነዉ። በዚህ ጉባኤ ከአስተናጋጃ ከጃፓን ሌላ ዬኤስ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ጀርመን፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይና የአዉሮጳ ኅብረት ተወካዮች ጉባኤዉን በመካፈል ላይ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1Iuv7
Japan G7 Gipfel
ምስል Reuters

ሩስያ ከዩክሩይን ጋር በገባችበት ዉዝግብ በተለይም ክሪሚያን ወደ ራስዋ ግዛት መጠቅለልዋን በመቃወም፤ ከአንድ ዓመት በፊት ከቡድኑ እንድትገለል መደረጉ ይታወቃል። G7 በመባል የሚታወቁት በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃገራት እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር 1970ዎቹ በዓለም ተከስቶ በነበረዉ የኤኮኖሚ ቀዉስ ምክንያት በጎርጎረሳዉያኑ 1975 ዐም እንደተቋቋመና ካናዳ በ1996 ሩስያ ደግሞ 1998 ዓ,ም ቡድኑን እንደተቀላቀሉ ይታወቃል። ከሁለት ዓመት ገዳማ በፊት ግን ሩስያ በዩክሪንይን ምክንያት ከቡድኑ እንደተገለለች ይታወቃል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ