የቡድን ሀያ ጉባኤ ፍፃሜ
ሰኞ፣ ሰኔ 21 2002ማስታወቂያ
መሪዎቹ የምጣኔ ሐብት ቀውስን ለማስተካከል የየበኩላቸውን ዕርምጃዎች እንደሚወስዱም አስታውቀዋል ። ጉባኤው እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጉባኤዎች ሁሉ ተቃውሞ እና አመፅ አልተለየውም ። ፖሊስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከተቃዋሚዎች ጋር የተጋጨ ሲሆን ትናንት ከሰዓት በኃላ 605 ሰዎችን አስሯል ። ተቃውሞውን ለመከላከል የቶሮንቶ ፖሊስ በከተማይቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አስለቃሽ ጢስ ተጠቅሟል ። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል
።
አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ