የቡሩንዲ ዉዝግብ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2008ማስታወቂያ
ከአስር ዓመታት በፊት በእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ የነበረችዉ ቡሩንዲ ፕሬዝደንቷ ሕገመንግሥቱ ከሚፈቅዳለቸዉ በላይ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ከወሰኑበት ጊዜ አንስቶ ሰላሟን አጥታለች። እንዲያም ሆኖ ፕሬዝደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ርምጃቸዉን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎች ሳይበርዱ በተካሄደዉ ምርጫ ተመልሰዉ ስልጣን ላይ ከወጡ ወዲህም ተቃዉሞዉ ቀጥሏል፣መንግሥትም የኃይል ርምጃዎች በመወስድ እየተተቸ ይገኛል። ቡሩንዲ ወደእርስ በርስ ጦርነት ልትገባ ትችላለች በሚል የአፍሪቃ ኅብረት ወደዚያ ሰላም አስከባር ለመላክ ማቀዱ ጠንካራ ተቃዉሞ ከመሪዎቿ ገጥሞታል። መንግሥት አሸባሪዎች ከሚላቸዉ ተቃዋሚዎቹ ጋር እንዲነጋገር የተመቻቸዉ የኢንቴቤዉ ድርድር እና የቡሩንዲ ከአፍሪቃ ኅብረት ጋር መፋጠጥን በሚመለከት ሸዋዬ ለገሠ ናይሮቢ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን አነጋግራለች።
ፋሲል ግርማ/ሸዋዬ ለገሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ