የበርሊን ግንብ የፈረሰበት ሀያኛ ዓመት
ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2002ማስታወቂያ
ጀርመንን ለሁለት ከፍሎ የቆየው የበርሊን የግንብ አጥር ፈረሰ ። የዚህ ግንብ መናድ ለሁለቱ ጀርመኖች ውህደት መንገድ በመጥረግና በዓለም ዙሪያ የኮምኒዝምን ስርዓት መንኮታኮት በማፋጠን በዓለም ታሪክ ልዩ ቦታን ይይዛል ። ይህ ዕለትም ዛሬ በርካታ የዓለም መሪዎች በተገኙበት በዋና ከተማይቱ በበርሊን እየተከበረ ነው ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የዛሬ ሀያ ዓመት የሆነውን ወደ ኃላ መለስ ብሎ ያስቃኘናል ። ግንቡ ሲፈርስ የነበሩ ኢትዮጵያያንም ትውስታቸውን ያካፍሉናል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ