የበርሊኑ የእስልምና ጉባኤና የሚኒስትሩ አስተያየት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 27 2003ማስታወቂያ
የአሁኑ ጉባኤም ከወትሮው በተለየ የብዙዎችን ትኩረት የሳበና ያነጋገረም ነበር ። የዚህ ምክንያቱም አዲሱ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንስ ፔተር ፍሪድሪሽ እስልምና የጀርመን አካል ነው የሚለው አባባል መሰረት የለውም ሲሉ የሰጡት አስተያየት ክርክር ባስነሳ ሰሞን ጉባኤው መካሄዱ ነበር ። ሆኖም ሚኒስትሩ ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ በዚህ አባባላቸው ለማለት የፈለጉትን በማብራራት የተፈጠረውን ቅሬታ ለማርገብ ሞክረዋል። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የጀርመን የእስልምና ጉባኤና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት ያስከተለውን ቅሬታ ይዳስሳል ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ