1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊኑ የቱሪዝም ትርኢት

ዓርብ፣ መጋቢት 2 2008

የዘንድሮዉ የበርሊን የቱሪዚም ትርኢት የበርካታ ሀገር ጎብኚዎች ስጋት የተሰማበት ነዉ። ወደቱኒዚያ፤ ቱርክ እና ግብፅ ተለትሮዉ በርካታ ጎብኚዎች የሚጓዙ ቢሆንም አሁን ግን የፀጥታ ይዞታ ስላሰጋቸዉ ቁጥራቸዉ መቀነሱ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1IBpM
Berlin Tourismus-Messe ITB Sao Tome und Prinz
ምስል DW/C. Vieira

[No title]

ያም ሆኖ ሁሉም የአዉሮጳ እና የሰሜን አሜሪካንን መንገደኞች በገፍ ወደየሀገሩ እየሳበ እንዲጎበኙ ለማድረግ ይጥራል። በተቃራኒዉ አዉሮጳዉያኑና አሜሪካዉያኑ ዜጎቻቸዉ ወደሌሎች ሃገራት ለጉብኝት መሄዳቸዉን ትተዉ በየሀገራቸዉ በቢሊየን የሚቆጠረዉን ዩሮና ዶላር የእረፍት ጊዜ ጉብኝት ወጪ ቢያፈስ ይመኛሉ። ኢትዮጵያም አሁን የሚጎበኟትን ቱሪስቶች ቁጥር በዕጥፍ ለማሳደግ ማቀዷን አመልክታለች። በርሊን በሚካሄደዉ የቱሪዝም ትርኢት ላይ የገበያ ሽሚያዉም አንዱ አካል እንደሆነ በስፍራዉ ተገንኝቶ የተመለከተዉ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ