የቆጵሮስ የገንዘብ ቀውስና መዘዙ
ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2005ማስታወቂያ
የአውሮፓ ህብረት ለቆጵሮስ ያወጣውን የብድርና የገንዘብ እርዳታ ስምምነት የሃገሪቱ ፓርላማ ውድቅ ካደረገው በኋላ ፣ ህብረቱ በጉዳዩ ላይ የሚነጋገረው ኒቆስያ አማራጭ የመፍትሄ እቅዶችን ካቀረበች ብቻ መሆኑን አስታወቀ ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የህብረቱ ባለሥልጣን ኒቆስያ ተጨባጭ አማራጮችን እስካላቀረበችለት ድረስ ህብረቱ በጉዳዩ ላይ ዳግም እንደማይመክር ተናግረዋል ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የአውሮፓ ህብረት ፣ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ለቆጵሮስ ከቅድመ ግዴታ ጋር 10 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር ተስማምተው ነበር ። በቅድመ ግዴታው መሠረት የኒቆስያ መንግሥት ከሃገር ውስጥ 5.8 ቢሊዮን ዩሮ እንዲያሰባስብ ተጠይቋል ። ስለ ቆጵሮስ የገንዘብ ቀውስና መዘዞቹ የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግረናል ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ