አቶ ማሙሸት ታሰሩ
ሰኞ፣ መጋቢት 25 2009ማስታወቂያ
የቀድሞ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ እና ወንድማቸው መታሰራቸውን ታናሽ ወንድማቸው ለዶቼቬለ ተናገሩ ። ሁለቱ ወንድሞቻው የተያዙት አቶ ማሙሸት ጠበል ይጠቀሙበት ከነበረው ሰሜን ሸዋ ውስጥ ከሚገኘው የምንጃር ሸንኮራ ጠበል ቦታ መሆኑን የአቶ ማሙሸት ወንድም ተናግረዋል ። አቶ ማሙሸት የት እንደሚገኙ እስካሁን በትክክል እንደማያውቁ እና ፍርድ ቤት አለመቅረበቻውን ወንድማቸው ገልጸዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ