1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ የቺሊ አምባገነን መሪ ፒኖሼ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 1999

የቀድሞዉ የቺሊ አምባገነን መሪ አጎስቶ ፒኖሼ መሞታቸዉ በተሰማ እለት በሺህ የሚቆጠሩ የአገሪቷ ተወላጆች ደስታቸዉን ለመግለጽ በከተማቷ አደባባይ ወጥተዉ እንደነበር

https://p.dw.com/p/E0hd
አጎስቶ ፒኖሼ
አጎስቶ ፒኖሼምስል dpa - Report

ባንጻሩ ደጋፊዎቻቸዉ የፒኖሼ ሲታከሙበት በነበረዉ እና ህይወታቸዉ አለፈ በተባለበት ሆስፒታል አቅራብያ በመሰብሰብ ሃዘናቸዉን ገልጸዋል። ፒኖሼ እ.አ 1973 እስከ አ.ም 1990 ድረስ ቺሊን በመምራት በቆዩበት ዘመን ህዝቡን በመከፋፈል ቢያንስ 3500 ያህል ህዝብ በግፍ ተገድሏል ወይም እስካሁን የደረሱበት አይታወቅም። ከ10ሺህ በላይ ደግሞ የስቃይ ቅጣት ደርሶባቸዋል ወይም ከአር ተሰደዋል።
መስከረም 1/ 19973 አ.ም የዛሪ የዛሪ 33 አመት ግድም ነበር። ጀነራል አጉስቶ ፒኖሼ ተከታዮቻቸዉን ከጎናቸዉ በማድረግ በግዜዉ የሶሻሊስት ርዮተ አለም ተከታይ የነበሩትን የአሪቷን መሪ Salvador Allendeን የመንግስት ግልበጣ ያካሄዱት።
እ.አ 1915 አ.ም በ Valparaiso በምትባለዉ የባህር ጠረፍ የተወለዱት ፒሼ በ17 አመታቸዉ ነበር የዉትድርና ትምህርታቸዉን የጀመሩት። ታድያ በአገራቸዉ የመንግስት ግልበጣ ባደረጉበት ወቅት የጦሩ ዋነኛ መሪ በመሆን በህዝብ ላይ ከባድ ጭካኔ በተሞላበት ህዝብን ጨፍጭፈዋል። ፒኖሼ የአሪቷን ከተቆጣጠሩ በኳላ በራድዮ ባሰሙት የጭካኔ ንግግራቸዉ
«በዛሪዉ ዕለት የአገሪቷ የጦር ሃይል እና የጸጥታ ተቆጣጣሪ ሃይል አገሪቷን ከብጥብጥ ነጻ ለማድረግ የአገር ወዳድነት ተግባር ፈጽመዋል»

ፒኖሼ እና ተከታዮቻቸዉ የመንግስት ግልበጣ ባደረጉ ልክ በሶስተኛዉ ሳምንት ፒኖሼ የአገሪቷ ፕሪዝደንት መሆናቸዉን አስታወቁ። ከዚያም ግዜ ጀምሮ ፒሼ በጦርነት ዉስጥ እንደሚገኙ ነበር በየግዜዉ የሚናገሩት። በሳቸዉም ትዕዛዝ 3000 ሺህ በላይ ተቃዋሚዎቻቸዉ ተገድለዋል። በመቀጠል ከሺህ በላይ እስካሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም። ከ 28,000 ሺህ በላይ ህዝቦች በስቃይ ተገርፈዋል፣ እንግልት ደርሶቫቸዋል። ፒኖቺየቶ አገሪቷን ያለ ህዝብ ምርጫ እንዲሁም በአንባ ገነን አመራር 27 አመታት ከቆዩ በኻላ እ.አ 1990 አ.ም ከስልጣናቸዉ በገዛ ፈቃዳቸዉ ለቀቁ። ስልጣናቸዉን በገዛ ፈቃዳቸዉም ሲለቁም ለህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በምንም አይነት ወንጀል ተጠያቂ መሆን እንደሌለባቸዉ አስታዉቀዉ እና ቃል አስገብተዉ ነበር።

የአገሪቷ የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አንባ ገነኑን መሪ ለብዙ ግዜ ለፒኖሼ ከፍተኛ የጡረታ ገንዘብ መበስጠት እና ችሎት እንዳይቀርቡ እገዛ አድርጎላቸዋል። ታድያ ፒኖሼ ከስልጣን ከለቀቁ ከስምንት አመት በኳላ እ.አ 1998 አ.ም በብሪታንያ ዉስጥ በበለንደን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ይኸዉም የስፔን ተወላጅ የሆነዉ ጠበቃ ፒኖሼን ህገወጥ የሆነ የጦር መሳርያ ንግድ፣ በተለያዩ የዉጭ አገሮች ዉስጥ ህገወጥ የሆነ በባንክ የገንዘብ ክምችት እንዳላቸዉ፤ እንዲሁም ቀረጥ ለብዙ ግዜ አለመክፈላቸዉን በሚያሳይ ክስ አንስቶባቸዉ ነበር። በመጨረሻም ፒኖሼ ወደ ቺሊ እንዲዛወሩ ተደርገዉ የሰባዊ ህጎችን በመጣስ በሚል ተጨማሪ ክስ ተመስርቶባቸዉ ሳለ ችሎት ለመቆም የሚያበቃ ጤና ስላልነበራቸዉ እስከለተ ሞታቸዉ ድረስ በቁም እስር ላይ ነበሩ።
በልብ ህመም ባለፈዉ እሁድያረፉት የ 91 አመቱ ፒኖሼ በቺሊ ዋና ከተማ በሳንቲያጎ ባለ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸዉ እንደ ነበርም ታዉቋል። የቺሊ መንግስት ቃል አቀባይ እንዳስታወቀዉ ዛሪ ማክሰኞ በዋና ከተማዋ በወታደራዊ ስነ ስርአት በቤተሰቦቻቸዉ የቀብሩ ስርአት እደሚፈጸም ታዉቋል።