1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀኝ አክራሪዎች ጥቃት በጀርመን

ዓርብ፣ ኅዳር 8 2004

የዉጪ ዝርያ ያላቸዉን ዘጠኝ ሰዎችና አንዲት ፖሊስን ሲገድሉ፥ ሌሎችን ሲያቆስሉ ፥ ለመግደል ሲያደቡ አስራ-አንድ ዓመት ካስቆጠሩ በሕዋላ ሰሞኑን ባጋጣሚ ተይዘዋል

https://p.dw.com/p/RxMN
ከተገደሉት በከፊልምስል picture alliance/dpa

የጀርመን የፖለቲካ ሐያሲያን የጀርመን የፍትሕ ሥርዓት «ቀኝ ዓይኑ እዉር ነዉ»-የሚል የቆየ ሥላቅ አላቃቸዉ።መልዕክቱ ግራ-አክራሪዎች፥ ሙስሊም ፅንፈኞች ወይም ሌሎች ብጤዎቻቸዉን እግር፥ በእርግር እየተከታተለ በመያዝ-ማጋለጡ የተመሠከረለት የጀርመን የፀጥታ መዋቅር የቀኝ ፅንፈኞችን እንቅስቃሴና ጥቃት ችላ ይላል-ማለት ነዉ።የጀርመን ቀኝ ፅንፈኞች የዉጪ ዝርያ ያላቸዉን ዘጠኝ ሰዎችና አንዲት ፖሊስን ሲገድሉ፥ ሌሎችን ሲያቆስሉ ፥ ለመግደል ሲያደቡ አስራ-አንድ ዓመት ካስቆጠሩ በሕዋላ ሰሞኑን ባጋጣሚ ተይዘዋል።ይሕ ሐቅ ነባሩን ብሒል ዳግም ቀስቅሶ የጀርመን ትልቅ ሰሞናዊ ርዕሥ አድርጎታል።የቀኝ ፅንፈኞቹ ጥቃትና መዘዙ የጀርመን ባለሥልጣናትን ያሳሰበ መስሏል። ሥለ ጉዳዩ ይልማ ሐይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ