1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽትራዉስ ከሐን ስንብትና አይ.ኤም.ኤፍ

ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2003

ግዙፍን የአለም ገንዘብ ድርጅት ላለፉት ሰወስት አመታት ከላይ ለመዘወር ያበቃቸዉ የእድገት፥ዉጤት-ስኬት፥ ቀና መንገድ አጉዞ አጉዞ ፕሬዝዳትነትን አጎናፅፎ ከኤሊሴ ቤተ-መንግሥት ዶላቸዋል ነበር የብዙዎች-ግምት-ተስፋ። የሳቸዉ ጥረትም።ቁል ቁል ተሽቀንጥረዉ ዘብጥያ አረፉ

https://p.dw.com/p/ROuu
የአይ.ኤም.ኤፍ ሕንፃምስል ullstein bild - Imagebroker.net

በሴት መድፈር ወንጀል የተከሰሱት የዓለም ገንዘብ ድርጅት (IMF) የበላይ ሐላፊ ዶሞኒክ ሽትራዉስ ካሕን ሥልጣናቸዉን ለቀቁ።በተጠረጠሩበት ወንጀል ባለፈዉ እሁድ ኒዮርክ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የታሰሩት ሽትራዉስ ካሕን በጠበቃቸዉ በኩል ይመሩት ለነበረዉ ድርጅት እንዳስታወቁት ግዙፉን የገንዘብ ተቋም መምራት አይችሉም።በገንዘብ ድርጅቱ ዉስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸዉ ሐገራት ሽትራዉስ ከሐንን የሚተካዉን ሐላፊ ለመሰየም እየተከራከሩ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ የዜና መልዕክቶች አሰባስቧል።

እንዲሕ እንደ ከዕሁድ በሕዋላዉ ባልነበሩበት ዘመን ጋዜጠኞች በጣሙን የሐገራቸዉ ልጆች DSK-በሚል የስምቸዉ አፅሕሮት ይጠሩ-ያቆለጳጵሷቸዉም ነበር።62 ዘመን ወጡ-ወጡ በሰዓታት ስሕተት ቁል ቁል ተንከባለሉ።«ኤ.ኤፍ.ፒ ሽትራዉስ ካሕን በወሲብ ጥቃት በመከሰሳቸዉ ምክንያት ሥልጣናቸዉን መልቀቃቸዉን ዘግቧል።»

አሏቸዉ የያኔ አወዳሽ አሞጋሾቻቸዉ።እዉቅ የሕግ ባለሙያ፥ ኢኮኖሚስት፥ ሙሉ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር፥ ፖለቲከኛ ሚንስትርም ነበሩ።ግዙፍን የአለም ገንዘብ ድርጅት ላለፉት ሰወስት አመታት ከላይ ለመዘወር ያበቃቸዉ የእድገት፥ዉጤት-ስኬት፥ ቀና መንገድ አጉዞ አጉዞ ፕሬዝዳትነትን አጎናፅፎ ከኤሊሴ ቤተ-መንግሥት ዶላቸዋል ነበር የብዙዎች-ግምት-ተስፋ። የሳቸዉ ጥረትም።ቁል ቁል ተሽቀንጥረዉ ዘብጥያ አረፉ።

ዶክተር ዶሞኒክ ሽትራዉስ ካሕን።የተከሰሱባቸዉን አስገድዶ የመድፈር፥ አካል የመጉዳት፥ እና ተያያዥ ወንጀሎችን መፈፀም-አለመፈፀማቸዉ በርግጥ ገና በፍርድ ቤት አልተረጋገጠም።የፖለቲካኛነት ጉዞ፥ የመሾም መሸለማቸዉ ክብር-ማዕረግ ሥም-ዝና ግን ከእንግዲሕ ነበር ነዉ።ሥልጣናቸዉም የቀድሞ።

Superteaser NO FLASH USA Frankreich IWF Dominique Strauss-Kahn vor Gericht
ሽትራዉስ ካሕንምስል dapd

የአለም ገንዘብ ድርጅትን የሐላፊነት መንበር ማን-ይረከብ ነዉ-የሐይለኛዉ አለም የከእንግዲሕ ጥያቄ፥ ክርክር።አንዳድ ያዉሮጳ ሐገራት በተለይም የሽትራዉስ ካሕን ሐገር ፈረንሳይ ሽትራዉስ ካሕንን የሚተካዉ ሰዉ ሲሆን ከፈረንሳይ ይሕ ቢቀር ከአዉሮጳ መሆን አለበት ባይ ናቸዉ። የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም እንደ አዉሮጳዊ ወደ አዉሮጳ ማድላታቸዉ አልቀረም።ግን በቀጥታ አልተናገሩትም።«ከዚሕ» በሚል ቃል ገደም-ደም አድርገዉ ገለጡት።

«የሽትራዉስ ካሕን ዘመነ-ሥልጣን ያበቃ እንዳልነበር ማሰብ አለብን።ሥለዚሕ (የእሳቸዉ) ምትክ የሚፈለገዉ በዚሕ ዘመነ-ሥልጣን ጊዜ በመሆኑ ከዚሕ ይሁን ይባል ይሆናል።እንደሚመስለኝ እየበለፀጉ ካሉት ሐገራት ይሁን የሚል ክርክር እና አስተሳሰብም መቅርቡ አይቀርም።ብዙ ነገር መነሳቱ አይቀርም።»

አዳዲሶቹ ሐብታሞች ወይም በመበልፀግ ላይ ያሉ የሚባሉት ሐገራት ግዙፉን የገንዘብ ተቋም የሚመራዉ የኛ ሰዉ መሆን አለባት ባይ ናቸዉ።በተለይ BRICS በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠሩት ብራዚል፥ ሩሲያ፥ ሕንድ፥ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ለአለም ምጣኔ ሐብት እድገት አስተዋፅኦ አበርክቱ መባል ብቻ ሳይሆን ምጣኔ ሐብቱን የመዘወሩ ሥልጣንም ይድረሰን ባዮች ናቸዉ።

የቀድሞዉ የብራዚል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሴልሶ አሞሪም እንደሚሉት ደግሞ አዉሮጳ-አሜሪካ ብቻ የሚባልበት ዘመን አክትሟል።

«ይሕ ዘመን ያለፈበት ነዉ።አለም በቡድን ሰባት ብቻ ትመራ በነበረበት ጊዜ የነበረ ነዉ።ዛሬ ይሕ ተቀባይነት የለዉም።ከደቡብ አፍሪቃ በስተቀር የብሪክስ ሐገራት ለአለም ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ብድር ከሚሰጡ አስር-ሐገራት መካካል ናቸዉ።ከነሱ መሐል ገሚሶቹ ደግሞ ለአለም ምጣኔ ሐብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከሚያደርጉ አስር ሐገራት ዉስጥ ናቸዉ።ከነዚሕ መሐል ብራዚል አንዷ ናት።»

Verhaftung Strauss-Kahn Medien Frankreich
ምስል AP

የሐብታሞቹ ሐገራት ክርክር፥ ዉይይት ቀጥሏል።የሽትራዉስ ካሕን የፍርድ ቤት ሙግትም እንዲሁ።


ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ