የሽታይንብሩክ አስተያየትና ትችቱ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 25 2005ማስታወቂያ
አንጋፋው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ ፖለቲከኛና የመጪው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ፔር ሽታይን ብሩክ ሰሞኑን የሰጡት አስተያየት እዚህ ጀርመን እያነጋገረ ነው ። ሽታይንብሩክ የጀርመን መራሄ መንግሥት ደሞዝ መሻሻል አለበት ፣ በመጪው ምርጫ የሚፎካከሯቸው የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተዋቂ ፖለቲከኛ ለመሆን የበቁት ሴት በመሆናቸው ነው ማለታቸው በራሳቸው ፓርቲ አባላት ጭምር አስተችቷቸዋል ። የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሽታይንብሩክ ስለሰጡት አወዛጋቢ አስተያየትና አስተያየቱ ስለሚያሳድርባቸው ተፅዕኖ የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ ጠይቀናል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ