1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብር ጥቃት ስጋት በሰሜን ምዕራባዊ አፍሪቃ

ዓርብ፣ ጥር 20 2008

ቡርኪና ፋሶ መዲና ዋጋዱጎ በሚገኝ ሆቴልና ምግብ ቤት ላይ የሽብር ጥቃት ከተፈፀመ ሁለት ሳምንት አስቆጠረ። በዚህ ጥቃት 30 ሰዎች ሲሞቱ፤ ሦስት አሸባሪዎች ተገድለዋል። ጥቃቱን ከጣሉት መካከል ሁለቱ ወይም ሦስቱ ሳያመልጡ እንዳልቀረ ተዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/1Hlus
Burkina Faso, Soldaten nach Terroranschlag
ምስል Reuters/J. Penney

[No title]

ከሦስት ወራት በፊት ማሊ መዲና ባማኮ በሚገኝ ሆቴል ላይ እንዲሁ የአሸባሪ ጥቃት መድረሱ ይታወቃል። በቱኒዝያም የሽብር ጥቃት ተጠናክሮዋል። በኒጀርና በናይጀርያም የሽብር ጥቃት በየቀኑ የሚታይ ክስተት ሆኖዋል። በሌላ በኩል እራሱን እስላማዊ ቡድን ብሎ የሚጠራዉ ቡድን እና አልቃይዳን የመሳሰሉ አሸባሪ ቡድኖች ፉክክር መያዛቸዉ ይስተዋላል።
ሴኔጋል ሊጣል ይችላል የተባለን የአሸባሪ ጥቃት ለመከላከል በከፍተኛ ጥበቃ ላይ ትገኛል። የምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ሃገር ባለስልጣን መሥርያ ቤት ሆቴሎች ቁጥጥራቸዉን እንዲያጠብቁ ሕዝቡም እንዲጠነቀቅና በንቃት እራሱን እንዲጠብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

Mali Geiselnahme Hotel in Bamako Befreiung von Geiseln
ባማኮ ማሊ-ጥቃትምስል Imago

በትዕዛዙ መሰረት ሆቴሎች በዋጋዱጉና ባማኮ ከደረሰዉ ዓይነት ጥቃት መከላከል ይኖርባቸዋል። ይደረግ የተባለዉ የደህንነት ጥበቃ ደንብን ያላከበረ ሆቴሉ የመዘጋት ማለት የመታሸግ እድል እንደሚከተለዉ ነዉ የተመለከተዉ። ይህ ማሳሰብያ ይፋ እንደተደረገ በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ በሃገሪቱ ከሽብር ጥቃት ጋር ተያያዥነት ሳይኖራቸዉ አይቀረም የተባሉ 900 ተጠርጣሪ ማስረጃዎች መንግሥት እጅ ደርሰዋል። ምንም እንኳ እንስካሁን ሃገሪቱ ምንም ዓይነት የሽብር ጥቃት ደርሶ ባያዉቅም፤ በሴኔጋል የሽብር ጥቃት ይደርሳል የሚለዉ ሥጋት እየጨመረ መጥቶአል። ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል እንደሚሉት ከሆነም ስጋቱ አለ።

« በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ሥጋቱ ከፍተኛ ነዉ። ከዚህ ሌላ አሸባሪዎች በኢንተርኔት የመገናኛ መረብ በኩል ድርጅቶች የሚያካሂዱት ፕሮፖጋንዳ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖዋል። ሌላዉ ምንም እንኳ መንግስት ከፍተኛ ጥንቃቄ ቢያደርግም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ገንዘብ እየሰጡ ኃይማኖት ዉስጥ ጣልቃ ይገባሉ።»
የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታትና ተጠሪዎች በጥብቅ እንደተከታተሉት፤ በሰሜን አፍሪቃ የማግሪብ ሀገራት የሚታየዉ የኧል-ቃይዳ እንቅስቃሴ ወደ ምዕራብ አፍሪቃ እየተስፋፋ ነዉ። ለዚህም በቡርኪና ፋሶ የተፈፀመዉ የአሸባሪ ጥቃት ዋነኛ ማስረጃ መሆኑን በጽንፈኞች ጉዳይ ላይ ምርምር የሚያካሂዱት ፈረንሳዊ ዋሲም ናስር ይገልፃሉ። እንደ ዋሲም ናስር በሰሜናዊ አፍሪቃ በሚገኙት የሙስሊም ሃገሮች የሚገኘዉ ኧል-ቃይዳ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ከሌሎች የሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ፀብ ላይ ነበር። አሁን ግን ኧል-ቃይዳ ከአንድ የአልጀርያ ጽንፈኛ ቡድን ጋር አብሮ እየሰራ ነዉ።
ቦርቸርስ ዘገባ መሰረት ኧል-ቃይዳ በማሊ እንዲሁም በከፊል አልጀርያ ዉስጥ እየተንቀሳቀ ነዉ። ይህ ቡድን የሽብር ሥራዉን እና የቁጥጥር ግዛቱን በቀጣይ ወደ ደቡብ እያሰፋ ነዉ። በዚህ ዓላማዉ ቡርኪናፋሶ የመጀመርያ ዒላማዉ ነበረች። የቡርኪናፋሶ አዋሳኝ ሃገሮች ኧል-ቃይዳ በቀጣይ ጥቃቱን የት ይጥል ይሆን ሲሉ ይጠይቃሉ። ኧል-ቃይዳ በዋጋዱጉና በባማኮ ሆቴሎች ላይ ጥቃትን ያደረሰዉ ኧል-ሞርአቢቶኔ ከተሰኘዉ ጽንፈኛ ቡድን ጋር ተጣምሮ ነዉ። በጥቃቱ በርካታ የዉጭ ሃገር ዜጎችንም ገድሎአል። በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዳግም ዓይን ዉስጥ ለመግባት በቅቶአል። በሁለቱም ጥቃቶች ላይ የነበሩት ጥቃት አድራሾች ወጣቶች እንደ ነበሩ እና ሁሉም ደግሞ እንዳልተገደሉ፣ ምናልባትም ሳያመልጡ እንዳልቀረ ነዉ የተመለከተዉ። እዚህ ላይ እዉነታዉ ይላሉ ናስር፣ ኧል-ቃይዳ ተዳክሞአል ተብሎ መታሰቡ ነው።

«ዋጋዱጉ ጥቃት በተጣለበት ወቅት አንድ ጥቃት አድራሽ የኧል-ቃይዳ ፕሮፖጋንዳ አቅራቢ ሰሜናዊ አፍሪቃ ከሚገኝ « አክሚ» ከተባለዉ ጽንፈኛ ቡድን ጋር ስልክ ተደዋዉሎ፤ ለኧል-ቃይዳዉ መሪ ለኧል-ዛዋሪ ዳግም ታማኝነቱን በቃለ ማኃላ አረጋግጦአል። ኧል-ቃይዳ «አክሚ» የሚባለዉ አሸባሪ ቡድን እያሳደረ የመጣዉ ጫና መጨመሩ አሳስቦታል። «አክሚ» በናይጀርያ በቦኮሃራም ታማኝነትን አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። «አክሚ» በሌሎች አፍሪቃ ሃገራትም ይገኛል።»
ሰሜን ምዕራብን አፍሪቃ ሃገራት ከሽብር ጥቃት ለመከላከል ፖሊስና ጦር ሰራዊቱ ጥረት ላይ ይገኛሉ። ኧል-ቃይዳና «እስላማዊ መንግሥት » የተባሉት ፅንፈኛ የሽብር ቡድኖች፤ ተጨማሪ ደጋፊዎችን ያገኛሉ የሚል ስጋትም አለባቸዉ። የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በርካታ የሃገራቸዉ ወጣቶች በእነዚህን አክራሪ ቡድኖች ፕሮፖጋንዳ እንዳይታለሉ ሰግተዋል።
« በርግጥ ብሩህ የወደፊት ተስፋ የሌላቸዉ ወጣቶች፤ ለአሸባሪዎች ቀላል መሳርያ ናቸዉ። እንደ መንግሥትና ዉሳኔ አስተላላፊ አካል ለወጣቱ የወደፊት ተስፋ መስጠት የኛ ኃላፊነት ነዉ። »

የንስ ቦርቸርስ / አዜብ ታደሰ

Burkina Faso Senegals Präsident Macky Sall
የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልምስል Reuters/J. Penney
Tunesien Terrorgefahr Britische Touristen
የቱኒዝያዉ ጥቃትምስል picture-alliance/AA/M. Amine Ben Aziza


አርያም ተክሌ