የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉ ፀረ-ሽብር ርምጃ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 10 2008ማስታወቂያ
ይሁንና የሽብሩን ጥቃት ለመከላከል የሚወሰደዉ ፀረ-ሽብር ርምጃ ሙሉ በሙሉ ዉጤታማ አለመሆኑ ነዉ የሚታየዉና የሚነገረዉ። ጥቃትና የአፀፋ ጥቃቱ ቀጥሎ፤ አሸባሪዎቹም ሳይጠፉ ስማቸዉን በመቀያየር የፀረ ሽብሩ ዘመቻም መቋጫ ሳያገኝ እንደዉም ፅንፈኝነት እየገነነ አገር እየወደመ፤ ሽብሩ አሜሪካ፤ አፍሪቃ፤ መካከለኛዉ ምስራቅ ብሎ መኃል አዉሮጳ ደርሷል። በሌላ በኩል የፀረ- ሽብሩን ዘመቻ ተከትሎ የተለያዩ መንግሥታት የፀረ-ሽብር አዋጅን አዉጥተዉ የሰብዓዊ መብትን፤ የመናገርና የፕሬስ ነፃነትን፤ እንደሚደፈጥጡ ይህንኑ ርምጃቸዉንም አጠናክረዉ መቀጠላቸዉ በየጊዜዉ አቤት የሚሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት መግለጫ የአደባባይ ምሥጢር ነዉ። ይህ እንወያይ መሰናዶ የዓለማችን የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉን የፀረ-ሽብር ርምጃ ይቃኛል። ዉይይቱ በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድን በመቃወም በተፈጠረው ግጭት እጃቸው አለበት በተባሉትና በአሸባሪነት በተፈረጁት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በተመለከተም ተወያዮች የሰጡት አስተያየት ተካቶበታል።
ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫዉን ማዕቀፍ በመጫን ይከታተሉ።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ