1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ለብርቱካን ሚዴቅሳ

ሐሙስ፣ ጥር 21 2001

ትናንት ከፓርቲዉ ፅሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ የተሰበሰቡት የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች ወይዘሪት ብርቱካን የታሰሩበትን አንደኛ ወር ሻማና ጧፍ በማብራት አስበዉታል

https://p.dw.com/p/GjWs
ኢትዮጵያምስል AP GraphicsBank/DW

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸዉን የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን እንዲለቅ አዲስ አበባ የሚኖሩ የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች ጠየቁ።ትናንት ከፓርቲዉ ፅሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ የተሰበሰቡት የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች ወይዘሪት ብርቱካን የታሰሩበትን አንደኛ ወር ሻማና ጧፍ በማብራት አስበዉታል።የፓርቲዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ወይዘሪት ብርቱካንን ለማስለቀቅ ፖለቲካዊ፥ ሕጋዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎቻቸዉን አንደቀጠሉ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።