1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሸቀጦች ዋጋ ንረት በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 3 2007

ዘንድሮ አሮጌው ዓመት ተገባዶ አዲሱ መጣሁ በሚልበት ወቅት ቀደም ሲል በሀገሪቱ የዝናብ እጥረትን ተከትሎ የተከሰተው ድርቅ እና የዋጋ ንረት መከታተላቸው በርካቶችን ለችግር ዳርገዋል። በተለይ ዝቅተኛ ኹኔታ ኑሮን የሚገፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጫናው ከፍተኛ እንደሆነባቸው በመግለጥ እያማረሩ ነው።

https://p.dw.com/p/1GTHp
Bildergalerie Äthiopien Teff
ምስል DW/J. Jeffrey

[No title]

ጤፍ፣ በርበሬ፣ የመሳሰሉት ግብዓቶች እጅግ ዋጋቸው ከማሻቀቡም በላይ በአንዳንድ ቦታዎች የዘይት አቅርቦት ፈጽሞ እንደሌለ እየተገለጠ ነው። የተለያዩ የማኅበረሰቡ ክፍሎች የዋጋው ጭማሪ ምክንያታዊ አይደለም ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በእለታዊ ኑሯቸው ላይም አሉታዊ ጫና መፍጠሩን ገልጠዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ