የሶሪያ ተቃዋሚዎችና ወቅታዊው ሁኔታ10 ኅዳር 2005ሰኞ፣ ኅዳር 10 2005የሶርያ ተቃዋሚዎች በያዝነው ወር መጀመሪያ በቃጣር ዶሃ በመሰባሰብ ሁሉም ተቃዋሚዎች አንድ የህብረት ግንባር መፍጠራቸው፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሶርያ ግጭት እልባት የሚያገኝበትን መንገድ እንዲያፈላልግ ተስፋ ሰጭ ነው ተብሎ ይታመናል።https://p.dw.com/p/16lvSምስል AFP/Getty Imagesማስታወቂያ የተመሰረተው የሶርያ ተቃዋሚዎች ህብረት አብዛኛውና ዋና ዋና ተቃዋሚ ቡድኖች ያቀፈ በመሆኑ በአረብ ሃገራትና በምዕራባውያን ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ማግኘቱ መልካም ጅምር ተደርጎ ተወስዷል። በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ የተመሰረተውን ህብረት የሚቃወሙ ወገኖች ብቅ ማለታቸው እያነጋገረ ነው። ነብዩ ሲራክ ከጅዳ ዝርዝሩን ልኮልናል። ነብዩ ሲራክ አርያም ተክሌ