የሶማልያ አገናኝ ቡድን በጣልያን
ዓርብ፣ ሰኔ 5 2001ማስታወቂያ
ከፍጻሜ በኋላ እንደተገለጠዉ በፕሪዝዳንት ሼኽ ሸሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራዉ የሶማልያ የሽግግር መንግስት፤ በሃገር አቀፍ ማህበረሰብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅ፤ በአፍሪቃ ህብረት በአረብ ሊግ እና በሙስሊም አገራት ጉባኤ እዉቅና ያገኘ መሆኑን ገልጠዉ ተጨባጭ እገዛ እንደሚያሻዉም አስገንዝበዋል። በሌላ በኩል ጣልያንን በመጎብኘት ላይ ያሉት የወቅቱ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር የሊቢያዉ መሪ መሃመድ ጋዳፊ በሶማልያ የባህር ወንበዴዎችን ለመከላከል የተደረገዉን ዉይይት አስመልክቶ የባህር ዉንብድና ከሽብርተኝነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለዉ እና ሶማሌዎች የባህር በራቸዉን ማስጠበቅ መብታቸዉ መሆኑን መግለጻቸዉ ተጠቅሶአል። ዝርዝሩን ተክለዝጊ ገብረየሱስ ከሮማ አጠናቅሮልናል
ተክለዝጊ ገብረየሱስ/ አዜብ ታደሰ/ሸዋዬ ለገሠ