1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ የባህር ላይ ወንበዴዎች ለፍርድ በጀርመን

ዓርብ፣ ሰኔ 4 2002

በአለማቀፉ የባህር መንገድ ላይ የሚንሳፈፍ መርከቦችን የጠለፉ 10 የሶማሌ የባህር ላይ ወንበዴዎች ለፍርድ እዚህ ጀርመን ሃንቡርግ ከተማ መቅረባቸዉ ተገልጾአል።

https://p.dw.com/p/NoFV
ምስል picture-alliance/ dpa

የጀርመንን መርከብ ጠልፈዉ በኒዘርላንዱ የባህር ሃይል እጅ ከፍንጅ የተያዙት የባህር ላይ ወንበዴዎች በኔዘርላንድ በእስር ቆይተዉ ሳለ ነዉ በጀርመን ጥያቄ ወደ ጀርመን ለፍርድ የተዛወሩት። በጀርመን ለባህር ላይ ወንበዴዎች ፍርድ የመስጠት ሂደት ከ 600 አመት በኻላ ይህ የመጀመርያ እንደሆንም ተገልጾአል። የዶቸ ቬለዉ ባልደረባ ሉድገር ሻዶምስኪ የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።


ሉድገር ሻዶምስኪ /ይልማ ሃይለሚካኤል፣ አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ