የሶማሊያ ፖሊሶች መጥፋትና እንድምታው
ሰኞ፣ ሐምሌ 26 2002ማስታወቂያ
በኢትዮዽያ ሁርሶ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለሁለት ወራት ስልጠና የወሰዱ 1ሺህ ያህል የሶማሊያ ፖሊሶች በእርግጥ ከኢትዮዽያ ምድር ወጥተዋል። ሞቃዲሾ ግን አልደረሱም። እንደብዙዎች እምነት ፖሊሶቹ አክራሪ ቡድኖችን ሳይቀላቀሉ አይቀርም። የጀርመን መንግስት የበጀት ድጋፍ በኢትዮዽያ የሰለጠኑት የሶማሊያ ፖሊሶች ደባዛቸው የመጥፋት ጉዳይ እያነጋገረ ነው። በተለይም ጀርመን ስልጠናውን በተመለከተ ለመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አለማሳወቋ ሁለቱን ወገኖች እያሟገተ ይገኛል። ስልጠናው በኢትዮዽያ እንዲሰጥ መደረጉ ሌላው ችግር እንደነበርም የፖለቲካ ተንታኞች ገለጸዋል።
መሳይ መኮንን
አበበ ፈለቀ
አርያም ተክሌ