1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ሠላምና የፀጥታዉ ምክር ቤት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 9 2001

ፓን እንደሚያምኑት ሶማሊያን ከከፋ ትርምስ ለማዉጣት የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊትን ማጠናከሩ ጠቃሚ ነዉ

https://p.dw.com/p/GJDI
የፀጥታዉ ምክር ቤትምስል Samir Huseinovic

የሶማሊያን ሠላም የሚያስከብር አለም አቀፍ ሠራዊት የሚዘምትበት ሁኔታ እንደሌለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አስታወቁ።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደሚሉት በሶማሊያ የሚከበር ሠላም ሥለሌለ ሠላም አስከባሪ ማዝመት አያስፈልግም፥ ይዝመት ቢባልም ሠራዊት ለማዋጣት ፍቃደኛ የሆነ ሐገር የለም።ፓን እንደሚያምኑት ሶማሊያን ከከፋ ትርምስ ለማዉጣት የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊትን ማጠናከሩ ጠቃሚ ነዉ።የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎችን የሚወጋ ጦር ለማዝመት ግን አለም ባንድ አብሯል።አለም አቀፉ ጦር ወንበዴዎቹን ከባሕር ክልል እስከ ሶማሊያ የአየርና የየብስ ግዛት ድረስ ዘልቆ እንዲወጋ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ደንግጓል።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።