1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያው ጦርነትና በምስራቅ አፍሪቃ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር

ረቡዕ፣ ኅዳር 30 2002

በህግ አልባዋ ሶማሊያ የሰፈነው ስርዓተ አልበኝነት ምስራቅ አፍሪቃ ዋነኛ የወንጀል ማዕከል እንድትሆን እገዛ እያደረገ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/KyHL
ምስል Nigora Bukharizoda

የድርጅቱ የአደንዛዥ ዕፅና የወንጀል ጉዳዮች ተከታታይ ቢሮ ሀላፊ አንቶንዮ ማርያ ኮስታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እንዳስታወቁት በአካባቢው የተስፋፋው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሌሎች ህገ ወጥ ዕንቅስቃሴዎች ለችግሩ መጠናከር አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው ። በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታዎች አስተባባሪ ቢሮ በበኩሉ በሶማሊያ የተደራጀ ወንጀል መስፋፋት የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን ስጋት ውስጥ እንደጣለው አስታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ