1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዝግጅት 09.11.15

ሰኞ፣ ጥቅምት 29 2008

ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ማህበር አትሌት ማሬ ዲባን የሴቶች ማራቶን ኮከብ ሲል ሸለመ ። የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት አመታት ከዋና ዋና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ውጭ ሆነ።

https://p.dw.com/p/1H2Mj
Novak Djokovic
ምስል picture-alliance/dpa/Y. Valat

የስፖርት-ዝግጅት-09.11.15

በቻይና ሻንጋይ ከተማ በተካሂደው በጎርጎሮሳዊው 2015 የቻይና ሻንጋይ ዓለም አቀፍ ማራቶን ሩጫ ውድድር 19 አመቱ ኢትዮጵያዊ አትሌት ቶላ ሹራ 2 ሰአት 08 ደቂቃ 53 ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ሆኗል። ኬንያዊው አትሌት  ፖል ኪፕቹምባ 2 ሰአት 07 ደቂቃ 14  ሰከንድ በመጨረሽ ውድድሩን አሸንፏል ። ያለፈው አመቱ የውድድሩ አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊው ስትፍን ሞኩካ ደግሞ 2 ሰአት 07 ደቂቃ 40 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ወጥቷል ። በሴቶች ተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስትኛ ሆነዋል አትሌት ለተብርሀን ሀይሌ 2 ሰአት 28 ደቂቃ 11 ሰከንድ በመገባት ሁለተኛ ራህማ ቱሳ 2 ሰአትከ 33 ደቂቃ 57 ሰከንድ በማስመዝገብ ሶስትኛ ደረጃ አግኝታለች ። ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው የ31 አመትዋ ኬንያዊት አትሌት ሪል ኒግሪቱኪ ናት ። ውድድሩን በ2 ሰአት 26 ደቂቃ 23ሰከንድ ነው የጨረሰችው። ዝርዝሩን የለንደንዋ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ አዘጋጅታዋለች ።

ሃና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ