የስደተኞች ጥያቄ እና የአውሮጳ ጭንቀት
ረቡዕ፣ ጥር 11 2008ማስታወቂያ
ይሁንና በስደተኞች ጥያቄ ውዝግብ ላይ ያለችው ሀገር ፖለቲከኞች በአሁኑ ሰዓት ድንበር ይዘጋ አይዘጋ ክርክር ላይ ናቸው። ይሄው የስደተኞች ጉዳይ ዳቮስ -ሲውዘርላንድ ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ዋና የመወያያ ርዕስ ነው። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዩሀይም ጋውክ ዛሬ በተለይ የምስራቅ አውሮጳ ሀገሮች የስደተኞችን የተገን ጥያቄ በተመለከተ ትብብር እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። አሳሳቢው የስደተኞች ጉዳይን አስመልክቶ፤ በጀርመን እና በአጠቃላይ በአውሮጳ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ወኪሎቻችንን፤ ከበርሊን ይልማ ኃይለሚካኤልን እና ከብራስልስ ገበያው ንጉሴን አነጋግረናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል/ ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ