የስደተኞች ቀዉስና ስዊድን
ዓርብ፣ ጳጉሜን 6 2007ማስታወቂያ
እንደ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሐገራት ሁሉ ለስዊድን መንግሥት፤ ለተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ ለርዳታ ድርጅቶችና ለአጠቃላይ ሕዝቡ የስደተኞች ብዛት፤ የማስተናገጃዉ አቅምና ብልሐት አብይ የመነጋገሪያ ርዕሳቸዉ ነዉ። ስዊዲን በርካታ ስደተኞችን በመቀበል ከጀርመን ቀጥሎ ሁለተኛይቱ አዉሮጳዊት ሐገር ናት። በብዛት የሚገባዉ ሥደተኛ የሚስተናገድበትን ብልሐት በጋራ ለመፈለግ የሐገሪቱ መንግሥት እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ትናንት ተወያይተዉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።የሐገሪቱ ሕዝብ በፋንታዉ የርዳታ ድርጅቶች ላደረጉለት የድጋፍ ጥሪ አበረታች መልስ እየሰጠ ነዉ። የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ቴዎድሮስ ምሕረቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሠ