1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች ቀን የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሚገኙበት በጋምቤላ ታስቦአል።

ማክሰኞ፣ ሰኔ 13 2009

በጎርጎሮሳውያኑ 2016 ጦርነት እና ግድያን በመሸሽ በረሀብ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ሰበብ የተሰደደው ህዝብ ቁጥር 65.5 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ ቁጥር በዓለም የቅርብ ዘመን ታሪክ እጅግ ከፍተኛው ነው።

https://p.dw.com/p/2f3Ll
Sudanesische Flüchtlinge in Äthopien Flüchtlingslager
ምስል DW/Coletta Wanjoyi

Q&A mit UNHCR-Ethiopia - MP3-Stereo

የዓለም የስደተኞች ቀን በዓለም ዙሪያ ዛሬ ታስቦ ውሏል። እለቱን ምክንያት በማድረግ የተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ሃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ በሰጡት መግለጫ ለስደተኞች ደራሽ የሆኑ ሀገራትን አመስግነዋል። ሌሎች ሀገራትም የነርሱን ፈለግ እንዲከተሉ ተማጽነዋል። በጎርጎሮሳውያኑ 2016 ጦርነት እና ግድያን በመሸሽ በረሀብ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ሰበብ የተሰደደው ህዝብ ቁጥር  65.5 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ ቁጥር በዓለም የቅርብ ዘመን ታሪክ  እጅግ ከፍተኛው ነው። ከአፍሪቃ በርካታ ስደተኞችን በምታስናግደው በኢትዮጵያ የስደተኞች ቀን የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሚገኙበት በጋምቤላ ዛሬ መታሰቡን በኢትዮጵያ የ«UNHCR» ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። አቶ ክሱትን በስልክ አነጋግረናቸዋል። በቅድሚያ በኢትዮጵያ ምን ያህል ስደተኞች እንደሚገኙ ይገልጹልናል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

ኂሩት መለሰ 

ነጋሽ መሐመድ