«ኢትዮጵያዉያኑ በሰላም እንዲመለሱ እየጣርን ነዉ» የጂዳ ቆንስላ
ዓርብ፣ ሰኔ 16 2009ማስታወቂያ
በስዑድ አረብያ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሚኖሩ አንዳድ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ የመንን ወደ መሳሰሉ ሃገራት ከመፍለስ ይልቅ ወደ ሃገራቸዉ ቢመለሱ እንደሚሻል ቆንስላዉ ምክር ለግሶአል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያስቀመጠዉ ቀነ ገደብ ፤ ሊራዘም ይችላል ነገ መግለጫ ይወጣል የሚለዉ ተናፋሽ ወሬን ማረጋገጥ አይቻልም ፤ በስዑዲ መንግሥት በኩልም የምሕረት አዋጁ እዚህ ጋር ይቆማል ተብሎ መግለጫ አልተሰጠም ሲሉ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ተናግረዋል።
ቆንፅላ ጽ/ቤቱ መመለስ ለሚሹ ኢትዮጵያዉያን ሰነድ ከመስጠት ባሻገር ትራንስፖርት እንዲያገኙ ሁሉ ጥረት እያደረገ መሆኑም ታዉቋል።
በስዑድ አረብያ ሕገ-ወጥ የተባሉት ኢትዮጵያዉያንን ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የባሕር መስመር የሚያቀርብ አካል ካለ እድሉን ሰጥተናል ሲሉም አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ተናግረዋል።
መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመለሱ ዜጎች የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣል ። በዚህም ከስዑዲ አረብያ የሚፈናቀለዉ ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሩ ወደ ወገኑ ቢገባ እመክራለሁ ሲሉ አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ገልፀዋል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ