የስዊድን የአውሮጳ ህብረት የሚንስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢነት የስልጣን ዘመን
ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2001ማስታወቂያ
የስዊድን መንግስት ሚንስትሮችና የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ባለስልጣናት ስቶክሆልም ውስጥ ስብሰባ ተቀምጠው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ህብረቱ ሊሰራቸው ይገባል ባሉዋቸው ጉዳዮች መክረዋል። ስዊድን ለአየር ንብረት ለውጥና በፊናንሱ ቀውስ ሰበብ በህብረቱ አባል ሀገሮች ውስጥ ለተከተለው የስራ አጥነት ችግሮች መፍትሄ ለማፈላለጉ ጉዳዮች ቀዳሚውን ትኩረት እንደምትሰጥ የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ፍሬዴሪክ ራይንፌልት አስታውቀዋል።
ገበያው ንጉሴ/አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ