1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስኳር ፕሮጀክቱ ቀዉስ

እሑድ፣ ግንቦት 14 2008

በስድስት ዓመታት ዉስጥ ዐሥር ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎችን ገንብቶ በቢሊዮን የሚቆጠር የዉጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ የታቀደዉ የስኳር ፕሮጀክት ቀዉስ ገጥሞታል።

https://p.dw.com/p/1Is2X
Zucker
ምስል bit24 - Fotolia

የስኳር ፕሮጀክቱ ቀዉስ

የስኳር ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠዉ የኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች የሥራ አፈጻጸም ዘገባ ከታቀደዉ የአንዱም ፋብሪካ ሥራ ሳይጠናቀቅ ብድር የመክፈያዉ ወቅት መድረሱን ለምክር ቤቱ አርድቷል። በሀገር ዉስጥ የስኳር እጥረት መኖሩ እና ዋጋዉ መናሩ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ፋብሪካዎቹ ተጠናቀዉ ወደ ስኳርነት ይለዉጡታል ተብሎ የተተከለዉ አገዳ ደርሶ ወደ መበላሸት መቃረቡም ይነገራል። የተቆጠርና ገና ያልተቆጠረ ገንዘብ ብክነት የገጠመዉ ፕሮጀክት የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ የእንወያይ ርዕስ ነዉ። ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ