የስኳር በሽታና መዘዙ
ረቡዕ፣ ጥር 11 2003ማስታወቂያ
ጀርመን ዉስጥ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በስኳር ህመም ይሰቃያሉ። ዘመናዊዉ የህክምና አገልግሎት፤ መድሃኒቱና ሃኪም ቤት እጅግ ከሰለጠኑ ባለሙያዎች ጋ በሚገኝባት አዉሮፓዊት ጀርመን ይህን መሰሉን የጤና እክል መስማት ሊያስገርም ይችላል። እንደዉም ምርምርና የህክምና አገልግሎቱ በተስፋፋባት ሃብታም አገር ይህ የተከሰተ በሌሎች በህክምና ሙያ የሰለጠነ የሰዉ ኃይልም ሆነ የአቅም ድሃ በሆኑ አገራት የስኳር በሽታ በተጠቂዎቹ ላይ ምን ሊያደርስ እንደሚችል መገመቱም ይከብዳል።
ሸዋዬ ለገሠ