1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስብዓዊ መብት ይዞታ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2001

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማሻሻል የኢትዮጵያ መንግስት ትርጉም ያለው ዕርምጃ አልወሰደም ሲል ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሂዩመንራይትስ ዎች ወቀሰ ።

https://p.dw.com/p/GDG9
የሂዩመንራይትስ ዎች ወቀሳ

የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌን ስልሳኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው በሂዩመንራይትስ ዎች የአፍሪቃ ክፍል ከፍተኛ ተመራማሪ ክሪስ ላኪ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ እየተበላሸ የሄደውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ለማሻሻል ከመሞከር ይልቅ ፣ መንግስት የሚቀርብበትን ወቀሳና ክስ ማስተባበል ነው የሚቀናው ።