1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስርጭት ጊዜ ለውጥ

ሰኞ፣ ሰኔ 6 2003

ዶቼ ቬለ የአማርኛ አገልግሎት፤ የበርካታ አድማጮቹን ጥያቄ ከግምት በማስገባት እና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በጉዳዩ ላይ የተደረገውን ጥናት በመመርኮዝ የስርጭት ጊዜ ለውጥ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/RHZV

በዚሁ መሠረት ከሚያዚያ 2 ቀን 2003 ጀምሮ ከምሽቱ አንድ ሠዓት እስከ ሁለት ሠዓት ባለዉ ጊዜ የየዕለት ዝግጅቶቹን በሚከተሉት የሞገድ መስመሮች ያሰራጫል። በ17780 KHz - 16m፣ በ11835 KHz - 25m፣በ9800 KHz - 31m። ከ1957 አንስቶ በራድዮ የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ በዘመኑ ቴክኖሎጂም ከአድማጮቹ ይደርሳል። ማንኛውም አድማጭ ዝግጅቶቹን በድረ ገፅ፣ በፖድካስት፣ በፌስ ቡክ እና በትዊተርም መከታተል፣ መሳተፍም ይችላል።

ዓለምን ለመረዳት ዶቼ ቬለን ያድምጡ!