የስልጣን ጥል በኮንጎ ሬፓብሊክ 25 ታኅሣሥ 2004ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 25 2004በዴሞክራሲያዊት የኮንጎ ሬፓብሊክ በሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ዦሴፍ ካቢላ እና በዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ኤትየን ቺሴኬዲ መካከል ያለው የስልጣን ጥል ዛሬም እንደቀጠለ ነው።https://p.dw.com/p/13WBuኤትየን ቺሴኬዲ እና ዦሴፍ ካቢላምስል picture alliance/dpa/DW-Fotomontageማስታወቂያ ከ 11 ቀናት በፊት በኮንጎ ሬፓብሊክ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኃላ በአገሪቱ ምንም የተረጋጋ ነገር የለም። ምንም እንኳን የምርጫው አሸናፊ ዦሴፍ ካቢላ ቢሆኑም ቺሴኬዲ ምርጫው እንደተጭበረበረ እና እሳቸውም የፊታችን ዓርብ አዲሱ የኮንጎ ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሀላ እንዲፈጽሙ ጠይቀዋል። በአንፃሩ ካቢላ ዛሬ የፕሬዚደንትነት ቃለ መሀላቸውን ፈፀሙ ።