1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴኔጋል ምርጫና ዉጤቱ

ረቡዕ፣ የካቲት 21 1999

ባለፈዉ እሁድ በሴኔጋል የተካሄደዉ ምርጫ በታዛቢነት የተገኙት የምእራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አባላት በሴኔጋል የተካሄደዉ ፕሪዘደንታዊ ምርጫ ነጻ እና ትክክለኛ ነበር ሲሉ ገለጹ

https://p.dw.com/p/E0hF
የቀድም የሴኔጋል ጠቅላይ ሚ/ር የአሁኑ ፕሪዝደንት ዕጩ ኢድሪሳ ሴክ
የቀድም የሴኔጋል ጠቅላይ ሚ/ር የአሁኑ ፕሪዝደንት ዕጩ ኢድሪሳ ሴክምስል PA/dpa

ምርጫዉ በተካሄደ እለት የፕሪዝደንት አብዱላዬ ዋድ ደጋፊዎች የምርጫዉ አሸናፊ ሆነናል በማለት ደስታቸዉን ሲገልጹ ታይተዋል። በትናንትናዉ እለት በታተሙ የአገሪቷ ጋዜጦችም ዋዴ ማሸነፋቸዉን የሚገልጽ ዘገባም አዉጥተዋል፣ ነገር ግን የፕሪዝደንት ዋድ ተቀናቃኞች ዉጤቱ ተጭበርብሯል ሲሉ ቅሪታቸዉን ማሰማታቸዉን ቀጥለዋል። በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የAfrica Press Agency ጋዜጠኛን አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግራ ነበር ።