1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴቶች ጤናና መብት

ማክሰኞ፣ የካቲት 30 2002

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች የመብት ረገጣ ብቻ ሳይሆኑ ጤናቸዉን የሚጎዱ መሆናቸዉ እየታወቀ ይመስላል።

https://p.dw.com/p/MO8q
ምስል picture-alliance/ dpa

ሴቶች ላይ የሚፈፀመዉ ግርዛት ከጊዜያዊ ስቃይና ህመምነቱ ባሻገር በወሊድና ተያያዥ ጉዳዮች ወቅት የሴቶችን ጤና ለችግር የሚዳርግመሆኑን ተገንዝበዉ እንዲቆም የሚታገሉ ወገኖች ቁጥር ከፍ እያለ ነዉ። ከዓመታት በፊት በከንባታ ጠንባሮ አካባቢ ይፈፀም የነበረዉ ይህ ድርጊት አሁን አላስፈላጊነቱን በተገነዘቡ ወገኖች የተቀናጀ ጥረት ቀንሶ ወደሶስት ከመቶ ወርዷል። በተመሳሳይ በትግራይ 50በመቶ ሲቀንስ ባጠቃላይ በአገር ደረጃ ደግሞ 25በመቶ መድረሱ ይነገራል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ