የሴት የቀን ሠራተኞች አቤቱታ
ሰኞ፣ ሰኔ 11 2004ማስታወቂያ
በአንዳንድ የግል ህንፃ ተቋራጮች የሴቶችና የወንዶች የቀን ሠራተኞች ክፍያ እንዲስተካከል ተጠየቀ ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በግል ህንፃ ተቋራጮች የሚሰሩ አንዳንድ ሴቶች ለተመሳሳይ ሥራ የሚያገኙት ክፍያ ከወንዶች ያነሰ መሆኑ አግባበ አይደለም ሲሉ አማረዋል ። ሴት ሠራተኖቹ ለተመሳሳይ ሥራ እኩል ክፍያ ማገኘት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል ። ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው የሴቶች የህጻናትና የወጣቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ ችግሩ ተጠንቶ መፈታት እንዳለበት አስታውቋል ። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አዘጋጅቶታል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ