የሳዑዲ አረቢያ የምጣኔ ሐብት ተሐድሶ
ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2008ማስታወቂያ
የሳዑዲ አረቢያ ነገሥታት የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብታዊ አቋም ለመለወጥ ይረዳል ያሉትን አዲስ ዕቅድ በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።ራዕይ 2030 የተሰኘዉ ዕቅድ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እስካሁን ካለበት ከነዳጅ ዘይት ጥገኝነት ለማላቀቅና የምጣኔ ሕብቱን ምንጭ ለማስፋት ያለመ ነዉ።የንጉስ ሠልማን ወንድ ልጅ የምክትል አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሠልማን የ«አዕምሮ ልጅ» የተባለዉ ዕቅድ የሐገሪቱ ዜጎች በተለያዩ የምጣኔ ሐብት መስኮች እንዲሳተፉ፤የዉጪ ባለሙያዎችን ተክተዉ እንዲሠሩ፤የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር እና ሐገሪቱ ለዉጪ ባለሐብቶች ክፍት እንድትሆን የሚያደርግ ነዉ።ዕቅዱን ገቢራዊ ለማድረግም የተለያዩ የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ባዲስ መልክ ተዋቅረዋል።የካቢኔ ሹም ሽር ተደርጓልም።የሪያድ ነዋሪ ሥለሺ ሽብሩን ሥለዕቅዱ በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።
ሥለሺ ሽብሩ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ