የሳዑዲ ሴቶች ደስታውን እየገለጹ ነው
ረቡዕ፣ መስከረም 17 2010ማስታወቂያ
የሳዑዲ ዓረቢያ ሴቶች መኪና የማሽከርከር መብታቸውን ተጎናጸፉ ፡፡ ለዘመናት ከሌሎች ሀገሮች ሴቶች በተለየ መልኩ ተነፍገው የኖሩት መኪና የማሽከርከር መብታቸው እንዲከበር ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱል አብዱል አዚዚ መፍቀዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ትላንት ምሽት ይፋ አድርገዋል፡፡ የመኪና መንዳት መብታችን ይከበር የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ በማንሳት ግፋ ሲልም እያሽከረከሩ አደባባይ የወጡ የሳዑዲ ሴቶች ከዚህ በፊት ለእስር ተዳረገው እንደነበር ይታወሰል፡፡ ዛሬ ደስታቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡ሳዑዲ ዓረቢያን በዓለም አቀፍ መድረክ ሲወቅሷት የኖሩ ሀገራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለንጉሱ ውሳኔ አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ዝርዝሩን ያቀርብልናል።
ስለሺ ሽብሩ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ