የውጡልኝ አዋጅ ዳግም ተራዘመ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 19 2009ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረብያ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች ከሀገርዋ እንዲወጡ ያስቀመጠችውን ቀነ ገደብ ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመች። በጅዳ-ሳዑዲ አረብያ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በአምደ መረቡ ባሰራጨው ማስታወቂያ ህገ ወጥ የሚባሉ የውጭ አገር ዜጎች ሳውዲ አረብያን ለቀው የሚወጡበት ጊዜ ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ለተጨማሪ አንድ ወር ዳግም መራዘሙን ገልጧል። ቆንስላው ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ እና ቲኬት እንዲያዘጋጁ ጠይቋል። ዳግም ስለተራዘመው ስለዚሁ አዋጅ ጅዳ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነብዩ ሲራክ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ