የሳውዲ ርዳታ ለጋዛ ውጊያ ሰለባዎች
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001ማስታወቂያ
ታዛቢዎች ከልክ ያለፈና ያልተመጣጠነ ባሉት የእስራኤል የአየር፡ የምድር እና የባህር ጥቃት ከአክራሪው የሀማስ ድርጅት ዒላማዎች ጎን በርካታ ሴቶች፡ ህጻናትና ሽማግሌዎችም ተጠቂዎች ሆነዋል። ውጊያው በጋዛ አሳሳቢ ሰብዓዊ ችግር በመፍጠሩ የቆሰሉትን የማከሙ ተግባር ይበልጡን አዳጋች እንደሆነባቸው የሀኪም ቤቶች ሰራተኞች ሲገልጹ ይሰማል። የሳውዲ ዐረቢያ መንግስት፡ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ እንደገለጸው፡ ይህንኑ ችግር ለማቃለል በማሰብ ለሀኪም ቤቶች እገዛ የሚሆን ርዳታ ልኮዋል።