የተከሳሾቹ ጉዳይ በግልጽ ችሎት ይታያል፤
ረቡዕ፣ ጥቅምት 29 2010ማስታወቂያ
አስራ አንድ ልዑላዊ ቤተሰቦች ፣ ከሰላሳ በላይ ከፍተኛ ባለ ሀብቶች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናትን አስጠርጥሮ ለእስር የዳረገው ዘመቻ ፤ ሙስናን ከስር መሰረቱ የመንቀል የመጀመሪያው ምዕራፍ መሆኑ ተገልጧል ፡፡ በቀጣይ ምዕራፍም ከ አንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ባለስልጣናት እና ባለ ሀብቶች ጉዳያቸው ይታያል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የንጉስ ሰልማን እና የአልጋ ወራሹን ድርጊት አወድሰዋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ሼክ መሀመድ አላሙዲን በቢሊዮን ዶላሮች በሚገመቱ ሁለት ጉዳዮች ስማቸው መጠቀሱን የክሱን ሂደት የሚከታተሉ በሪያድ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ለዶቸ ቨለ ገልጸዋል። ።
ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋኅ መሐመድ