1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳን በርናርዲኖ ግድያና እስላማዊ መንግስት

ቅዳሜ፣ ኅዳር 25 2008

ራሱን «እስላማዊ መንግስት» በማለት የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ሳን ቤርናዲኖ 14 ሰዎች የገደሉት ጥንዶች ተከታዮቼ ነበሩ ሲል አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1HHzQ
USA Kalifornien Schießerei in San Bernardino
ምስል Reuters/M. Anzuoni

የጽንፈኛ ቡድኑ መግለጫ በድረ-ገጽ ሬዲዮ የተሰማው ከካሊፎርኒያ ግዛት ግድያው ከተፈጸመ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው። የ28 አመቱ አሜሪካዊ ሰይድ ሪዝዋን ፋሩቅ እና የ29 አመቷ ባለቤቱ ታሽፈን ማሊክ በሳን ቤርናዲኖ የፈጸሙት ግድያ በፌዴራል ምርመራ ቢሮ( FBI) እንደ ሽብር እየተመረመረ ነው። ማሊክና ባለቤቷ ራሱን «እስላማዊ መንግስ» ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ተነሳስተው የፈጸሙት ሊሆን ይችላሉ ሲሉ የአሜሪካን መንግሥት ባለስልጣናት ምንጮች አስታውቀዋል። ባለስልጣናቱ አሁን ድርጊቱን ራሱን «እስላማዊ መንግስት» ብሎ በሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ለመቀነባበሩ አልያም በቡድኑ ትዕዛዝ ለመፈጸሙ ማስረጃ አለመኖሩን ተናግረዋል። ፋሩቅ ግድያን ከባለቤቱ ጋር የፈጸመው በሥራ ባልደረቦቹ ላይ ነው።

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ