የሳልህ ሞት የሰላም ተስፋዉን ጨልሞታል፤
ረቡዕ፣ ኅዳር 27 2010ማስታወቂያ
በካይሮ የሰንዓ ማዕከል የስልት ጥናት ዳይሬክተር ለፈረንሳይ የዜና ወኪል እንደገለፁት፤ መሠረት የነበሩት ሳልህ ወደማይመለሱበት ስለሄዱ የየመን የፖለቲካ መፃኢ ዕድል አሁን ፍፁም ተቀይሯል። ባለፈዉ ቅዳሜ ነበር ጠንካራዉ የየመን ፖለቲከኛ ከሁቲ አማፅያን ጋር ለሦስት ዓመት የነበራቸዉን መቀራረብ ወደጎን ብለዉ፤ የተኩስ አቁም እና የተዘጉ መተላለፊያዎች ይከፈቱ ዘንድ «ጠላት» ከሚሏት ሳዉዲ ጋር አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ዝግጁነታቸዉን ይፋ ያደረጉት። በእርግጥም የእሳቸዉ መገደል የመን ዉስጥ የተጫረዉን እሳት የሚያግመዉ እንጂ የሚያጠፋዉ እንደማይሆን የሳዉዲ የፖለቲካ ተንታኞችም እያረጋገጡት እንደሆነ ነዉ ሪያድ የሚገኘዉ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩም የገለፀልን። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ስለሺ ሽብሩ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ