የሲድኒው የእገታ ጥቃት ማብቃት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2007የሲድኒ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ አንድሩ ስኪፒየን ቀደም ሲል እንዳስረዱት፣ ግለሰቡ ያገታቸው ሰዎች ቁጥር በግልጽ አልታወቀም ነበር።
« አንድ የጦር መሳሪያ የታጠቅ ግለሰብ በከተማይቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን አግቶዋል። ፖሊስ ስለእገታው እንደተነገረው ወዲያው በጥዋቱ በቦታው በመገኘት ሁኔታውን ተቆጣጥሮዋል። እገታው ሰላማዊ ፍፃሜ እንዲያገኝ በአሁኑ ጊዜ እየሰራን ነው። ይህ እገታ በሰላማዊ ዘዴ መፍትሔ እንዲያገኝ እንፈልጋለን፣ ይህንንም ለማረጋገጥ የሚቻለንን ሁሉ በማድረግ ላይ ነን። »
ታጋቾቹ ወደ 30 እንደሚጠጉ ይገመታል። አንድ ታጋቾች አንድ የእሥልምና እምነት የተጻፈበት ጥቁር ባንዴራ በቡና ቤቱ መስኮት እንዲይዙ መገደዳቸው በቴሌቪዥን የቀረበ ስዕል አሳይቶዋል። ይህም ከእገታው በስተጀርባ ፅንፈኛ ሙሥሊሞች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ስጋት መፍጠሩን ስለ አጋቹ ማንነት ወይም ዓላማ እስካሁን እንደማይታወቅ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቲም አቦት ገልጸዋል።
« የአጋቹን ዓላማ ገና አላወቅንም፣ መነሻው ፖለቲካዊ መሆን አለመሆኑንም አናውቅም፣ ምንም እንኳን ፖለቲካዊ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች ቢኖሩም። »
አጋቹ እስካሁን ያቀረበው ጥያቄ ስለመኖሩ መረጃ የሌለ ሲሆን፣ ቡና ቤቱን ያጠቁት የፖሊስ ኃላፊ አንድሩ ስኪፒየን አመልክተዋል። በመጨረሻ በወጡ ዘገባዎች መሠረት፣ አጋቹ በኦስትሬሊያ ተግን አግኝቶ የሚኖር የሀምሳ ዓመት የኢራን ተወላጅ መሆኑ ተገልጾዋል።
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ