1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን የመኖርያ ፈቃድና ኢትዮጵያዉያን

ሐሙስ፣ የካቲት 2 2009

በሱዳን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት ብዙ ገንዘብ ክፈሉ እንባላለን ሲሉ አማረሩ። አንድ የሱዳን ነዋሪ እንደጠቆሙት የሱዳን መንግሥት ከ 2017 ዓመት መጀመርያ ጀምሮ ለስድስት ወር መኖርያ መታወቅያ ከሁለትሺ በላይ የሱዳን መገበያያ ገንዘብ ፓዉንድ አምጡ እያለ መሆኑን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2XFpD
Sudan Neue Brücke über dem Nil
ምስል picture-alliance/dpa/P. Dhil

M M T/ Umstrittenes Aufenthaltsrecht Äthiopiens im Sudan - MP3-Stereo

 

ይሄ ደግሞ በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ 4000 ብር በላይ ነዉ፤ ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ራድዮ ጣብያ መልዕክት ያስተላለፉት ተናግረዋል። በሱዳን የሚኖሩት አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉና በየስድስት ወሩ ለመታወቅያ እየከፈሉ የሚኖሩ ናቸዉ። ፖሊስ ቀኑ ያለፈበት መታወቅያ አልያም መታወቂያ የሌለዉ ኢትዮጵያዊን ሲይዝ እስር ቤት አስገብቶ እስረኛዉ በታሰረበት ቦታ ስራ እየሰራ ቅጣቱን ከፍሎ እንደሚወጣና አሁን ግን መታወቅያዉን ለማሳደስ ከ 2000 ፓዉንድ በላይ እንደሚያስፈልግ በካርቱም ነዋሪ የሆኑት አንድ ኢትዮጵያዊ ተናግረዋል።

ስድስት መቶ የሱዳን ፓዉንድ ማለት ወደ  1000 የኢትዮጵያ ብር ማለት ነዉ ያሉን እኝህ ሰዉ፤ ከአራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ እና የሱዳን መንግሥታት ኢትዮጵያዉያን ወደ 100 ፓዉንድ እየከፈሉ መታወቂያ እንዲያወጡ ስምምነት ደርሰ እንደነበር አስረድተዋል። 

በሱዳን መዲና ካርቱም ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅርበት የሚሰሩትና በሱዳን የኢትዮጵያዉያን ማኅበረሰብ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳዉድ አልሴማን  የመኖርያ ፈቃድ በተመለከተ የሱዳን መንግሥት ያወጣዉን አዲስ ነገርን ለመጠየቅ ኤምባሴዉ ጉዳዩ ወደ ሚመለከተው የመንግሥት መስርያ ቤት ሄዶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ሱዳን መንግሥት ዘገባና እንደ ኢትዮጵያዉያኑ ግምት በሱዳን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዉያን በካርቱም ብቻ ወደ አምስት መቶ ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይገኛሉ። ኢትዮጵያዉያኑ ለመታወቅያ ለምን ይከፍላሉ? የሱዳን መንግሥት ወደ ሃገር ቤት እንዳይመልሳቸዉ ለስድስት ወራት የሚዘልቅ መታወቅያ የmm,ስጠት ሕግን ከአራት ዓመት በፊት በማዉጣቱ ነዉ ሲሉ መልሰዋል።

ኢትዮጵያዉያኑ « ገንዘቡን ከሱዳን ጋር ተሻርኮ የሚወስደዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነዉ »ይላሉ።  የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምስት ሳንቲም አይወስድም የሚሉት አቶ ዳዉድ በሃሳብ አይስማሙም። ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሱዳን የሚመጡት ለመኖር ሳይሆን ወደ ሌሎች ሃገሮች ለመሸጋገር መሆኑን አቶ ዳዉድ አክለዋል።  ዛሬም በርካታ ኢትዮጵያዉያን የኢትዮጵያን ኤንባሲ ድጋፍ እየጠየቁ ነዉ።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ