የሱዳንና የቻድ ስምምነት እና አዲሱ ዉጊያ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 28 2001ማስታወቂያ
የሱዳንና የቻድ መንግሥታት የሻከረ ግንኙነታቸዉን ለማሻሻል መስማማታቸዉ በተነገረ-በሰወስተኛዉ ቀን ዛሬ በሱዳን ይደገፋሉ የሚባሉ የቻድ አማፂያን ምሥራቅ ቻድ ዉስጥ አዲስ ዉጊያ መክፈታቸዉ ተዘግቧል።የአፍሪቃ ሕብረት የአማፂያኑን ጥቃት አዉግዟል።የሕብረቱ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሁለቱ ሐገራት በቅርቡ ዶሐ-ቀጠር ላይ የተፈራረሙት ሥምምነት ገቢራዊ እንዲያደርጉት ሕብረታቸዉ የሚችለዉን ሁሉ ያደርጋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ያነጋገራቸዉ የሕብረቱ የሰላምና የፀጥታ ኮሚሽን ሊቀመንበር አል ጋሲም ዋኔ እንዳሉት የቻድና የሱዳን ስምምነት ለአካባቢዉ ሠላም ጠቃሚ ነዉ።
Getacehew Tedla
Negash Mohamed
►◄