የሱዳኑ ፕሬዝዳት የአዲስ አበባ ጉብኝት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2001ማስታወቂያ
የሱዳኑ ፕሬዝዳት ኡመር ሐሰን አልበሽር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ ።አለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዢያ ያወጣባቸዉ አልበሽር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት አላማ በኢትዮ-ሱዳን የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ መካፈል ነበር።ፕሬዝዳት አል-በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትናንት ማምሻ በጋራ እንዳሉት የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ብይን በሁለቱ ጎረቤት ሐገራት ግንኙነት ላይ የሚያሳድረዉ ተፅኖ የለም።አል-በሽር እንዲታሰሩ ከተበየነባቸዉ ወዲሕ ከኢትዮጵያ ሌላ ኤርትራን፥ግብፅን፣ ሊቢያንና ቀጠርን ጎብኝተዉ ነበር።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
Tadesse Engdaw/Negash Mohammed/Aryam Abraha
►◄