1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ ርዳታ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 1999

የአውሮጳ ኅብረት ኮሚስዮን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ አስቸኳዩን የሰብዓዊ ርዳታ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ኮሚስዮኑ ለኢትዮጵያ አምስት፡ ለኤርትራ ደግሞ ስድስት ሚልዮን ዩር ርዳታ ለማቅረብ የወሰነው ከዓለም አቀፍ የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የርዳታ ተማጽኖ ጥሪ ከቀረበለት በኋላ መሆኑን አርያም ተክሌ ያነጋገረቻቸው የኮሚስዮኑ የውጭ ግንኙነት ቃል አቀባይ ወይዘሮ ክርስቲያነ ሁማን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/E0XL