የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አሰራር ሲፈተሽ
ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2003ማስታወቂያ
በዚሁ ወቅትም አሜሪካን በውጭ እና በሀገር ውስጥ ትፈፅማቸዋለች ሰለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከአንዳንድ አባል ሀገራት በኩል ጠንከር ያሉ ትችቶች ተሰንዝረዋል ። በምክር ቤቱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤይሊን ቻምበርሌይን ዶናሆ የሰብዓዊ መብት አያያዛችን እንከን የለሽ ነው ብለን አናምን ብለዋል ። በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዕምነት የዋሽንግተን አስተዳደር እነዚህን ትችቶች በገንቢነታቸው የሚቀበል ከሆነ ለሌሎች አገራት ማለፊያ አቅጣጫ የሚያስይዝ አርአያ ሊሆን ይችላል ። የዶቼቬለዋ ኡልሪከ ማስት ኪርሽኒንግ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ የአሜሪካንን የሰብዓዊ መብት ይዞታን መመርመሩን መነሻ በማድረግ ስለ ምክር ቤቱ አሰራር ያቀረበችውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።
ኡልሪከ ማስት ኪርሽኒንግ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ