1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዳርፉር

ሰኞ፣ የካቲት 9 2007

የሱዳን መንግሥት ጦር ባለፈው ጥቅምት በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍለ ሃገር በዳርፉር ከተማ በርካታ ሴቶችና ህፃናትን ደፍሯል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት አጋልጧል ።

https://p.dw.com/p/1EcXy
Sudan, Symbolbild Massenvergewaltigung
ምስል picture-alliance/Ton Koene

ድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ደረጃ መታየት ያለበትም ነው ሲል እሳስቧል ። HRW ያቀረበውን ይህን ዘገባ የሱዳን መንግሥት ሃሰት ሲል አስተባብሏል ።

መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ረቡዕ ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው ሴቶችና ልጃገረዶቹ የተደፈሩት ባለፈው ጥቅምት 20 ፣ 2007 ዓም ዳርፉር በምትገኘዋ ታቢት በተባለችው መንደር ውስጥ ነው ።እንደ ዘገባው ታቢት አካባቢ የተሰማራው የሱዳን መንግስት ሠራዊት አንድ ወታደራችን ተገድሏል በሚል በወቅቱ ከ36 ሰዓትት በላይ የወሰደ ጥቃት ነበር የፈፀመው ። ድርጅቱ ከሁለት ወር ምርመራ በኋላ ባወጣው ባለ 48 ገፅ ዘገባው እንዳተተው ወታደሮቹ ጥቃቱን ያደረሱትም ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ነበር ።የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ።

Sudan Angriff auf Flüchtlingslager in Khor Abeche 06.04.2014
ምስል Reuters

በዚሁ የበቀል እርምጃ በግዳጅ የተደፈሩት ሴቶችና ልጃገረዶቹ ቁጥር ቢያንስ 221 ይሆናል እንደ ሂዩመን ራይትስ ዋች ።አቶ ዳንኤል እንዳሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ እንደተደረገ ጉዳዩን ለማጣራት የጠየቀው በአካባቢው የተሰማራው የአፍሪቃ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል በመጀመሪያ ተከልክሎ ኋላ ላይ ግን ተፈቅዶለት ወደ አካባቢው ቢሄድም በነፃነት መረጃ ማግኘት አለመቻሉን ነው አቶ ዳንኤል የተናገሩት ።

HRW በዚህ በጅምላ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ላይ ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ በጎርጎሮሳዊው 2009 የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርን በዚሁ በዳርፉር በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀልና በዘር ማጥፋት የእሥር ማዘዣ ቆርጦባቸዋል ። ሆኖም የአፍሪቃ መንግሥታት ትዕዛዙን ለማስፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል ። አቶ ዳንኤል በተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትም በኩል ይህ የፍትህ ጥያቄ በፖለቲካዊ አቋም ምክንያት መልስ አለማግኘቱ አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል ።

Human Rights Watch Logo Flash-Galerie
ምስል Human Rights Watch

አቶ ዳንኤል እንደሚሉት በግዳጅ ለተደፈሩት የዳርፉር ሴቶችና ልጃገረዶቹ አስፈላጊውን የህክምናና የሥነ ልቡና እርዳታ ለማድረግም ሆነ ጉዳዩ እንዲመረመርና እንዲጣራ የሱዳን መንግሥት እንዲተባበር መደረግ ይኖርበታል ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ